እነዚህም ሁሉ በባሳንና በገለዓድ ግዛቶች፥ በዚያም በሚገኙ ታናናሽ ከተሞች እንዲሁም በሳሮን ምድር የግጦሽ ቦታ ባለበት ስፍራ ሁሉ ይኖሩ ነበር።
ኢያሱ 13:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ለጋድ ነገድ ቤተሰቦች ርስት ሆነው የተሰጡአቸው ከተሞችና መንደሮች እነዚህ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋድ ነገድ በየጐሣቸው የወረሷቸው ከተሞችና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጋድ ልጆች ርስት ከተሞቻቸውም መንደሮቻቸውም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጋድ ልጆች ርስት ከተሞቻቸውም፥ መንደሮቻቸውም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። በጠላቶቻቸውም ፊት ጀርባቸውን መልሰው ሸሹ፤ መንደሮቻቸውና ከተሞቻቸው በየወገናቸው ሆነዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋድ ልጆች ርስት ከተሞቻቸውም መንደሮቻቸውም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። |
እነዚህም ሁሉ በባሳንና በገለዓድ ግዛቶች፥ በዚያም በሚገኙ ታናናሽ ከተሞች እንዲሁም በሳሮን ምድር የግጦሽ ቦታ ባለበት ስፍራ ሁሉ ይኖሩ ነበር።
ከዮርዳኖስ ሸለቆ በተለይ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን መንግሥት ቅሬታ የሆኑትን ቤትሐራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን ተብለው የሚጠሩትን ጭምር ያጠቃልላል፤ በምዕራብ በኩል የሚዋሰናቸውም የዮርዳኖስ ወንዝ ሲሆን፥ በሰሜን እስከ ገሊላ ባሕር ይደርሳል።