ኢያሱ 10:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢያሱ፦ “የዋሻውን በር ከፍታችሁ በማውጣት እነዚያን አምስት ነገሥታት ወደ እኔ አምጡ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም፤ “ዋሻውን ከፍታችሁ እነዚያን ዐምስቱን ነገሥታት አውጥታችሁ አምጡልኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “የዋሻውን አፍ ክፈቱ፥ እነዚያንም አምስት ነገሥታት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም፥ “የዋሻውን አፍ ክፈቱ፤ እነዚያንም አምስት ነገሥት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም፦ የዋሻውን አፍ ክፈቱ፥ እነዚያንም አምስት ነገሥታት ከዋሻው ወደ እኔ አውጡአቸው አለ። |
ከዚህ በኋላ የኢያሱ ሰዎች ሁሉ በሰላም ተመልሰው እርሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ማቄዳ መጡ። ከዚህም የተነሣ በምድሪቱ በእስራኤላውያን ላይ ደፍሮ ቃል የሚናገር እንኳ አልነበረም።
ሳሙኤልም “ንጉሥ አጋግን ወደዚህ አምጣልኝ!” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ አጋግም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ፤ በልቡም “ሞት እንዴት መራራ ናት!” እያለ ያስብ ነበር፤