ዮሐንስ 9:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውር የነበረውም ሰው፥ “እርሱ ኃጢአተኛ መሆኑን እኔ አላውቅም፤ አንድ ነገር ዐውቃለሁ፤ ይኸውም እኔ ዕውር እንደ ነበርኩና አሁን ማየት እንደ ቻልኩ ብቻ ነው” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ኀጢአተኛ መሆኑን እኔ አላውቅም፤ ነገር ግን ዐይነ ስውር እንደ ነበርሁ፤ አሁን ግን እንደማይ ይህን አንድ ነገር ዐውቃለሁ!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም መልሶ “ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዐይን ሥውር እንደ ነበርሁ፥ አሁንም እንደማይ፥ ይህንን አንድ ነገር አውቃለሁ፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ሰው መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እርሱ ኀጢኣተኛ እንደ ሆነ እኔ አላውቅም፤ እኔ ዕዉር እንደ ነበርሁ፤ አሁን ግን እንደማይ ይህን አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም መልሶ፦ “ኃጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዕውር እንደ ነበርሁ አሁንም እንዳይ ይህን አንድ ነገር አውቃለሁ” አለ። |
በዚህ ምክንያት ዕውር የነበረውን ሰው እንደገና ጠርተው “አንተ እውነቱን በመናገር እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት።
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ይህ ምስክርነት በልቡ ውስጥ አለ፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክርነት ባለማመኑ ሐሰተኛ አድርጎታል።