ዮሐንስ 8:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ሰምቼ እውነቱን የነገርኋችሁን እኔን ለመግደል ቈርጣችሁ ተነሥታችኋል፤ አብርሃም ግን እንዲህ አላደረገም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የምነገራችሁን እኔን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በእግዚአብሔር ዘንድ የሰማሁትን እውነት የምነግራችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትሻላችሁ፤ አብርሃምስ እንዲህ አላደረገም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አሁን ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም። |
ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ ነገር አለኝ፤ ይሁን እንጂ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ለዓለም የምናገረው ከእርሱ የሰማሁትን ነው።”
እንዲሁም አብርሃም ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት አባት የሆነበትም ምክንያት በመገረዛቸው ብቻ ሳይሆን እርሱ ከመገረዙ በፊት የነበረውን እምነት በመከተላቸውም ጭምር ነው።
ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ ከቀሩት የእርስዋ ዘር ጋር ሊዋጋ ሄደ፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የሚጠብቁና ለኢየሱስ በታማኝነት የሚመሰክሩ ናቸው።
በጅራቱ የኮከቦችን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣላቸው፤ ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ልጅዋን ለመዋጥ አስቦ ዘንዶው ልትወልድ ወደተቃረበችው ሴት ከፊት ለፊትዋ ቆመ፤