ዮሐንስ 8:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ከመጀመሪያ አንሥቼ እንደ ነገርኳችሁ ነኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እስካሁን የነገርኋችሁ እኔ እርሱ ነኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ “አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም “ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “አንተ ማነህ?” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “በመጀመሪያ ነግሬአችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ፦ “አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም፦ “ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ። |
የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ወደ ዮሐንስ ልከው፦ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ባስጠየቁት ጊዜ የሰጠው ምስክርነት የሚከተለው ነው፤
ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ ነገር አለኝ፤ ይሁን እንጂ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ለዓለም የምናገረው ከእርሱ የሰማሁትን ነው።”