ዮሐንስ 8:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ ባለሥልጣኖችም “ ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ ማለቱ ራሱን ሊገድል ይሆን?” ተባባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም፣ “ ‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ ያለው ራሱን ሊገድል ይሆን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድም “‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ ማለቱ እራሱን ሊገድል ይሆን?” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም፥ “እኔ ወደምሄድበት እናንተ መምጣት አትችሉም የሚለን እርሱ ራሱን ይገድል ይሆን? እንጃ!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድም፦ “እኔ ወደ ምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም ማለቱ ራሱን ይገድላልን? እንጃ” አሉ። |
የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ወደ ዮሐንስ ልከው፦ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ባስጠየቁት ጊዜ የሰጠው ምስክርነት የሚከተለው ነው፤
ስለዚህ የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች እንዲህ ተባባሉ፦ “እኛ እንዳናገኘው ይህ ሰው ወዴት ሊሄድ ነው? ምናልባት በግሪኮች መካከል ወደ ተበተኑት አይሁድ ዘንድ ሄዶ አሕዛብን ያስተምር ይሆን?
አይሁድ እንዲህ አሉት፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም እንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ አይሞትም’ ትላለህ፤