ዮሐንስ 7:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮቹም “ይህ ሰው እንደሚናገረው ዐይነት ማንም ተናግሮ አያውቅም” ሲሉ መለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂዎቹም፣ “እንደዚህ ሰው፣ ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም” ሲሉ መለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘቦቹም “እንደዚህ ሰው ማንም ከቶ አልተናገረም፤” ብለው መለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌዎቻቸውም መልሰው፥ “ያ ሰው እንደ ተናገረው ያለ ከቶ ሰው አልተናገረም” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌዎቹ፦ “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም” ብለው መለሱ። |
ሰዎቹ ስለ ኢየሱስ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ፈሪሳውያን ሰሙ፤ ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለማስያዝ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎችን ላኩ።