ነህምያ፦ “ሂዱና ምርጡን ምግብ ብሉ፤ ጣፋጩን መጠጥ ጠጡ፤ ምንም ለሌላቸውም ላኩ፤ ይህ ቀን ለአምላካችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ኀይላችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።
ዮሐንስ 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “አንድም ነገር እንዳይባክን የተረፈውንም ፍርፋሪ ሰብስቡ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ከተረፈው ቍርስራሽ ምንም እንዳይባክን ሰብስቡ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “አንድም እንኳን እንዳይጠፋ የተረፈውን ቁርስራሽ አከማቹ፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፥ “ከቍርስራሹ ምንም የሚወድቅ እንዳይኖር የተረፈውን ቍርስራሽ አንሡ፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፦ አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ የተረፈውን ቍርስራሽ አከማቹ አላቸው። |
ነህምያ፦ “ሂዱና ምርጡን ምግብ ብሉ፤ ጣፋጩን መጠጥ ጠጡ፤ ምንም ለሌላቸውም ላኩ፤ ይህ ቀን ለአምላካችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ኀይላችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።
የተመሸጉ ከተሞችንና፥ ለም የሆነችውን ምድር፤ በመልካም ነገር ሁሉ የተሟሉ ቤቶችን፥ የውሃ ጒድጐዶችንና የወይን ተክል ቦታዎችን የወይራና ብዙ የፍሬ ዛፎችን ወረሱ፤ በልተው በመጥገብም ሰውነታቸውን አወፈሩ፤ በቸርነትህ በሰጠሃቸው መልካም ነገር ሁሉ ተደሰቱ።
ደግሞም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “አንድ ሀብታም ሰው ቤቱን የሚያስተዳድርለት መጋቢ ነበረው፤ ሰዎች ‘ይህ መጋቢ ንብረትህን ያባክናል’ ብለው ለሀብታሙ ሰው ከሰሱት።