ዮሐንስ 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “ተነሥ! አልጋህን ተሸከምና ሂድ!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “ተነሥ! መተኛህን ተሸክመህ ሂድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ “ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “ተነሥና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። |
ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ለማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ” ሽባውን ሰው “ተነሥና አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።
ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ለመደምሰስ ሥልጣን እንዳለው ማወቅ አለባችሁ” ብሎ ሽባውን ሰው፦ “አንተ ሰው ተነሥ፤ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ!” አለው።