ዮሐንስ 4:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሲሄድም አገልጋዮቹ በመንገድ አገኙትና “ልጅህ ድኖአል” ብለው ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድ ላይ እንዳለም፣ ባሮቹ አግኝተውት ልጁ በሕይወት መኖሩን ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሲወርድ ሳለ አገልጋዮቹ ተገናኙትና “ብላቴናህ በሕይወት አለ፤” ብለው ነገሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲወርድም አገልጋዮቹ ተቀበሉትና፥ “ልጅህስ ድኖአል” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ሲወርድ ሳለ ባሮቹ ተገናኙትና፦ ብላቴናህ በሕይወት አለ ብለው ነገሩት። |
አባትየውም ኢየሱስ “ልጅህ በሕይወት ይኖራል” ያለው በዚያኑ ሰዓት እንደ ሆነ ዐወቀ፤ ስለዚህ ከዚያን ቀን ጀምሮ እርሱና ቤተ ሰቡ ሁሉ በኢየሱስ አመኑ።