ዮሐንስ 4:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሠራሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑ እዩ! ምናልባት እርሱ መሲሕ ይሆንን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እርሱ ክርስቶስ ይሆን እንዴ?” አለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሠራሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክርስቶስ ይሆን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን? አለች። |
መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።
ሳሙኤልም ሳኦልን፦ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር ስለምትበሉ ከእኔ በፊት ወደ ማምለኪያው ቀድመህ ውጣ፤ ነገ ጧት በልብህ ያለውን ሁሉ ነግሬህ አሰናብትሃለሁ፤