ሟቹ አልዓዛርም እጆቹና እግሮቹ በመገነዣ እንደ ተገነዙ ከመቃብሩ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር፤ ኢየሱስም “ፍቱትና ተዉት ይሂድ!” አላቸው።
ዮሐንስ 20:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐንበስ ብሎም ወደ መቃብሩ ቢመለከት የከፈኑ ጨርቅ እዚያ ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አልገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጐንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ በፍታውን ብቻ ተቀምጦ አየ፤ ወደ መቃብሩ ግን አልገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዝቅም ብሎ ሲመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን አልገባም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጐንበስ ብሎም ሲመለከት በፍታዉን ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አልገባም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዝቅም ብሎ ቢመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ነገር ግን አልገባ። |
ሟቹ አልዓዛርም እጆቹና እግሮቹ በመገነዣ እንደ ተገነዙ ከመቃብሩ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር፤ ኢየሱስም “ፍቱትና ተዉት ይሂድ!” አላቸው።