La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 13:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም “እርሱ ይህን እንጀራ በወጥ አጥቅሼ የማጐርሰው ነው” አለ። ይህንንም ብሎ እንጀራ በወጥ አጠቀሰና የአስቆሮታዊው ስምዖን ልጅ ለሆነው ለይሁዳ አጐረሰው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም፣ “ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” አለው፤ ከዚያም ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም “እኔ የእንጀራ ቁራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” ብሎ መለሰለት። ቁራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ እኔ እን​ጀራ በወጥ አጥ​ቅሼ የም​ሰ​ጠው ነው” አለው፤ ያን ጊዜም እን​ጀራ በወጥ አጥ​ቅሶ ለስ​ም​ዖን ልጅ ለአ​ስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ሰጠው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም፦ “እኔ ቍራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” ብሎ መለሰለት። ቍራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 13:26
8 Referencias Cruzadas  

ቀናኢው ስምዖን፥ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ። አንዱ አስተያየት፥ ከቦታ ወይም ከሀገር ጋር ሲያያይዘው ሌላው ወገን ደግሞ ይሁዳን ውሸታም ወይም አታላይ ብሎ ለመስደብ የተሰጠ ቅጽል ነው ይላል።


በዚያን ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው አስቀሮታዊው ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆች ሄደና


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ከእኔ ጋር በሳሕኑ ውስጥ የሚያጠቅሰው ነው።


“ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ እነሆ፥ ከእኔ ጋር በማእድ ነው።


ይሁዳም ጉርሻውን እንደ ተቀበለ ወዲያውኑ ወጥቶ ሄደ፤ ጊዜውም ሌሊት ነበረ።