ዮሐንስ 12:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱ የተነሣ ከአይሁድ ብዙዎቹ እምነታቸውን እየተዉ በኢየሱስ ያምኑ ስለ ነበረ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም በርሱ ምክንያት ብዙ አይሁድ ወደ ኢየሱስ እየሄዱ ያምኑበት ስለ ነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአይሁድ ብዙዎቹ በእርሱ ምክንያት እነርሱን እየተዉ በኢየሱስ ያምኑ ነበርና ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአይሁድ ብዙዎች ስለ እርሱ እየሄዱ በጌታችን በኢየሱስ ያምኑ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአይሁድ ብዙዎች ከእርሱ የተነሣ ሄደው በኢየሱስ ያምኑ ነበርና። |
ሆኖም ከአይሁድ አለቆች እንኳ ብዙዎቹ በኢየሱስ አምነዋል፤ ነገር ግን ፈሪሳውያን ከምኲራብ እንዳያስወጡአቸው በመፍራት፥ በግልጥ አልመሰከሩለትም።