ዮሐንስ 11:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ያለው ጊዜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ አይሰናከልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ብርሃን አይደለምን? ከዚህ ዓለም ብርሃን የተነሣ ስለሚያይ በቀን የሚመላለስ አይሰናከልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም መልሶ “በቀን ውስጥ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ይገኙ የለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚሄድ አይሰናከልም፤ የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም መልሶ፦ “ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ |
እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።