ዮሐንስ 11:56 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም በቤተ መቅደስ ቆመው የኢየሱስን መምጣት ይጠባበቁ ስለ ነበር “ምን ታስባላችሁ? ወደ በዓሉ የሚመጣ አይመስላችሁምን?” እያሉ እርስ በእርሳቸው ይጠያየቁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስንም ይፈልጉት ነበር፤ በቤተ መቅደስም ቆመው፣ “ምን ይመስላችኋል? ለበዓሉ አይመጣ ይሆን?” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስንም ይፈልጉት ነበር፤ በመቅደስም ቆመው እርስ በርሳቸው “ምን ይመስላችኋል? ወደ በዓሉ አይመጣም ይሆንን?” ተባባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም ጌታችን ኢየሱስን ይፈልጉት ጀመር፤ በቤተ መቅደስም ቆመው እርስ በርሳቸው፥ “ምን ይመስላችኋል? ለበዓል አይመጣ ይሆን?” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስንም ይፈልጉት ነበር፤ በመቅደስም ቆመው እርስ በርሳቸው፦ “ምን ይመስላችኋል? ወደ በዓሉ አይመጣም ይሆንን?” ተባባሉ። |