ደቀ መዛሙርቱም “ጌታ ሆይ! አንቀላፍቶስ ከሆነ ይሻለዋል ማለት ነው” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱም፣ “ጌታ ሆይ፤ ተኝቶ ከሆነስ ይድናል” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱም “ጌታ ሆይ! ተኝቶ እንደ ሆነስ ይድናል፤” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱም፥ “አቤቱ፥ ከተኛስ ይነቃል፤ ይድናልም” አሉት።
እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ ተኝቶስ እንደ ሆነ ይድናል” አሉት።
እርሱም “ሁላችሁም ከዚህ ውጡ! ልጅትዋ አንቀላፍታለች እንጂ አልሞተችም!” አላቸው። እነርሱ ግን በማፌዝ ሳቁበት።
ኢየሱስ ይህን ካላቸው በኋላ፥ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቶአል፤ እኔ ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አለ።
ኢየሱስ ይህን የተናገረው ስለ አልዓዛር መሞት ነበር፤ እነርሱ ግን ስለ እንቅልፍ የተናገረ መስሎአቸው ነበር።