ኢዩኤል 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተዘራው እህል ሁሉ በዐፈር ውስጥ በስብሶ ቀርቶአል፤ እህል በመታጣቱ የእህል ማከማቻዎች ሁሉ ባዶ ሆነዋል፤ ጐተራዎችም ፈራርሰዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘሩ በዐፈር ውስጥ፣ በስብሶ ቀርቷል፤ ግምጃ ቤቶቹ ፈራርሰዋል፤ ጐተራዎቹም ተሰባብረዋል፤ እህሉ ደርቋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሩ በምድር ውስጥ ተበላሸ፥ እህሉ ደርቆአልና ጎተራዎቹ ባዶ ናቸው፥ ጎታዎቹም ፈርሰዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጊደሮች ከምሳጋቸው ጠፉ፤ ጎተራዎች ባዶ ሆኑ፤ ዐውድማዎቹም ፈራረሱ፤ እህሉ ደርቆአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘሩ በምድር ውስጥ በሰበሰ፥ እህሉ ደርቆአልና ጎተራዎቹ ባዶ ናቸው፥ ጎታዎቹም ፈርሰዋል። |
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?