ኢዮብ 6:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከባሕር ዳር አሸዋ ይበልጥ በከበደ ነበር፤ ስለዚህ ትዕግሥት የጐደለው ንግግሬ ሊያስገርምህ አይገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በከበደ፣ ኀይለ ቃሌም ባላስገረመ ነበር! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባሕር አሸዋ ይልቅ በከበደ ነበርና፥ ለዚህም ነው ቃሌ ደፋር የሆነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና፤ ነገር ግን ቃሌ ሐሰትን ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና፥ ስለዚህ ቃሌ ደፋር ሆኖአል። |
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤ አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤ እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል።