ከበረሓ የተነሣ ዐውሎ ነፋስ በድንገት መጥቶ ቤቱን በሙሉ በገለባበጠው ጊዜ ቤቱ በላያቸው ላይ ስለ ተደረመሰ ሞቱ፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።
ኢዮብ 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቹም የኑሮ ዋስትና አያገኙም፤ በአደባባይም የሚከራከርላቸው ስለማያገኙ ጥቃት ይደርስባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቹ የኑሮ ዋስትና የራቃቸው፤ በፍርድ አደባባይ ጥቃት የደረሰባቸው፣ ታዳጊ የሌላቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቹም ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ተረግጠዋል፥ የሚደርስላቸውም የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቻቸው ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ይቀጠቅጡአቸዋል፤ መከራም ያጸኑባቸዋል፥ የሚታደጋቸውም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹም ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ተረግጠዋል፥ የሚታደጋቸውም የለም። |
ከበረሓ የተነሣ ዐውሎ ነፋስ በድንገት መጥቶ ቤቱን በሙሉ በገለባበጠው ጊዜ ቤቱ በላያቸው ላይ ስለ ተደረመሰ ሞቱ፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
በደላችሁ ምን ያኽል እንደ በዛና ኃጢአታችሁም ምን ያኽል ከባድ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ደጋግ ሰዎችን ታስጨንቃላችሁ፤ ጉቦ እየተቀበላችሁ በየፍርድ አደባባዩ የምስኪኖችን ፍትሕ ታጣምማላችሁ።
እርሱም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ፈጥኖ በመሄድ በከተማይቱ መግቢያ በር ወደሚገኘው ፍርድ ሸንጎ ቀርቦ የሆነውን ነገር ሁሉ ለመሪዎቹ ይገልጣል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ከተማይቱ እንዲገባ ይፈቅዱለታል፤ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡትና በዚያ ይቈያል፤