ኢዮብ 26:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሙሉ ጨረቃውን ፊት ይጋርዳል፤ በደመና ይሸፍነዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናዎቹን በላዩ ዘርግቶ፣ የሙሉውን ጨረቃ ፊት ይጋርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዙፋኑን ፊት ይሸፍናል፥ ደመናውንም ይዘረጋበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዙፋኑን ፊት ይከድናል፥ ደመናውንም ይዘረጋበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዙፋኑን ፊት ይከድናል፥ ደመናውንም ይዘረጋበታል። |
ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይምጣ፤ በተራራው በማንኛውም በኩል ቢሆን ማንም ሰው አይታይ፤ በግ ወይም ከብት ማንኛውም እንስሳ በተራራው ግርጌ አይሰማራ።”
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ክብርና ዘለዓለማዊ ኀይል ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።