ኢዮብ 11:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሐሳብህ ‘ትክክለኛ ነኝ’ ትላለህ፤ ለእግዚአብሔርም ‘በፊትህ ንጹሕ ነኝ’ ትለዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክንም፣ ‘ትምህርቴ የጠራ፣ በዐይንህም ፊት የጸዳሁ ነኝ’ ትለዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ፦ ትምህርቴ የተጣራ ነው፥ በዓይንህም ፊት ንጹሕ ነኝ ትላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ፦ በሥራዬ ንጹሕ ነኝ በፊቱም ጻድቅ ነኝ አትበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ፦ ትምህርቴ የተጣራ ነው፥ በዓይንህም ፊት ንጹሕ ነኝ ትላለህ። |
አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን?
ጌታ ክርስቶስን በልባችሁ አክብሩት፤ ለሕይወታችሁም ጌታ አድርጉት፤ በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ።