La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 38:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም በኋላ ባለ ሥልጣኖቹ መጥተው ጠየቁኝ፤ እኔም ልክ ንጉሡ ያለኝን ብቻ ነገርኳቸው፤ እኔና ንጉሡ ስንወያይ የሰማ ማንም ስላልነበረ ከዚያ በኋላ ጥያቄአቸውንም አቆሙ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

መኳንንቱ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፤ እርሱም ንጉሡ ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው፤ ከንጉሡ ጋራ የተነጋገሩትን ነገር የሰማ አንድም ሰው ስላልነበረ፣ ከዚህ በላይ አላነጋገሩትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አለቆቹም ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፥ እርሱም ንጉሡ እንዳዘዘው እነዚህን ሁሉ ቃላት ነገራቸው። ነገሩም አልተሰማም ነበርና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ መጥ​ተው ጠየ​ቁት፤ ንጉ​ሡም እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ደ​ዚህ ቃል ሁሉ ነገ​ራ​ቸው። ነገ​ሩም አል​ተ​ሰ​ማ​ምና ከእ​ርሱ ጋር መነ​ጋ​ገ​ርን ተዉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አለቆቹም ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁ፥ ንጉሡም እንዳዘዘው እንደዚህ ቃል ሁሉ ነገራቸው። ነገሩም አልተሰማምና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 38:27
7 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ ቀረብ ብሎ “መንገድ ተሳስታችኋል፤ የምትፈልጓት ከተማ ይህች አይደለችም፤ ይልቅስ ወደምትፈልጉት ሰው እኔ ልመራችሁ ስለምችል ተከተሉኝ” ብሎ ወደ ሰማርያ መራቸው።


ባለ ሥልጣኖቹ እኔ ከአንተ ጋር መነጋገሬን የሰሙ እንደ ሆነ መጥተው ምን እንደ ተባባልን ይጠይቁሃል፤ ሁሉን ነገር ባትነግራቸው እንገድልሃለን ብለው ያስፈራሩሃል፤


ስለዚህ ‘በዚያ እንዳልሞት እንደገና ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ’ እያልኩ ስለምነው ነበር ብለህ ንገራቸው።”


እኔም ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ጊዜ ድረስ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ተዘግቶብኝ ቈየሁ።


ጳውሎስ እዚያ ከነበሩት ሰዎች እኩሌቶቹ ሰዱቃውያን እኩሌቶቹ ደግሞ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ዐውቆ “ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ከፈሪሳዊ የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ፤ እነሆ! አሁን በፍርድ ፊት የቀረብኩት በተሰጠው ተስፋና በሙታን ትንሣኤ ምክንያት ነው” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ በሸንጎው መካከል ተናገረ።