La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 33:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ለቀንና ለሌሊት መፈራረቅ፥ ለሰማይና ለምድር ቋሚ ሥርዓት የሰጠሁበትን ቃል ኪዳን ያልመሠረትሁ ከሆነ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የቀንና የሌሊት ኪዳኔን፣ የሰማይንና የምድርንም ሥርዐት ያጸናሁ እኔ ካልሆንሁ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እንዲህ ይላል፦ የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን የሰማይንና የምድርንም ሥርዓት ያላጸናሁ እንደሆነ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የቀ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን የሰ​ማ​ይ​ንና የም​ድ​ር​ንም ሥር​ዐት ያላ​ጸ​ናሁ እንደ ሆነ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን የሰማይንና የምድርንም ሥርዓት ያላጸናሁ እንደሆነ፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 33:25
9 Referencias Cruzadas  

ለምድር ብርሃንን እንዲሰጡ እነዚህን ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ አኖራቸው፤


ምድር እስካለች ድረስ፥ ለመዝራትና ለማጨድ፥ ለብርድና ለሙቀት፥ ለበጋና ለክረምት፥ ለቀንና ለሌሊት የማያቋርጥ ጊዜ ይኖራል።”


ጨረቃን የወቅቶች ምልክት እንድትሆን፥ ፀሐይ የሚጠልቅበትን ጊዜ እንዲያውቅ አድርገሃል።


ፍጥረቶች ሁሉ አገልጋዮችህ ስለ ሆኑ ትእዛዞችህ እስከ ዛሬ ጸንተው ቈይተዋል።


ምንጊዜም በማይፈርስ ድንጋጌ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም መሥርቶአቸዋል።


“ለአገልጋዬ ለዳዊት ዙፋን የሚወርስ ልጅ እንደምሰጠው የገባሁት ቃል ኪዳንና ለአገልጋዮቼ ለሌዋውያን ስለሚሰጡኝ አገልግሎት ያቆምኩላቸው ቃል ኪዳን ሊፈርሱ የሚችሉት ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዲመጡ ያቆምኩላቸውን ሥርዓት ከእናንተ መካከል ለማፍረስ የሚችል ሰው የተገኘ ከሆነው ነው።