“እናንተ ‘እግዚአብሔር በአባቶች በደል ልጆችን ይቀጣል’ ትላላችሁ፤ እስቲ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ራሳቸውን ይቅጣቸው፤ ይህ ከሆነ በደለኛነታቸውን ሊገነዘቡት ይችላሉ።
ኤርምያስ 31:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ዘመን፥ ‘አባቶች የበሉት ጎምዛዛ የሆነ የወይን ፍሬ፥ የልጆችን ጥርስ አጠረሰ’ እየተባለ የሚነገረው ምሳሌ ይቀራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ዘመን ሰዎች ዳግመኛ፣ “ ‘አባቶች በበሉት ጐምዛዛ የወይን ፍሬ፣ የልጆች ጥርስ ጠረሰ’ የሚለውን ምሳሌ አይናገሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ዘመን ሰዎች ዳግመኛ እንዲህ አይሉም፦ ‘አባቶች የሚጎመዝዝ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ፤’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ዘመን ሰው ዳግመኛ እንዲህ አይልም፦ አባቶች ጮርቃ የወይን ፍሬ በሉ፤ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ዘመን ሰው ዳግመኛ እንዲህ አይልም፦ አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ፥ |
“እናንተ ‘እግዚአብሔር በአባቶች በደል ልጆችን ይቀጣል’ ትላላችሁ፤ እስቲ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ራሳቸውን ይቅጣቸው፤ ይህ ከሆነ በደለኛነታቸውን ሊገነዘቡት ይችላሉ።
“ልጆቻቸው በሠሩት ወንጀል ወላጆች በሞት መቀጣት የለባቸውም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ወንጀል ልጆቻቸው በሞት አይቀጡ፤ እያንዳንዱ ሰው በሠራው ወንጀል በሞት ይቀጣ።