La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 31:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልጆቻችሁ ወደ አገራቸው ተመልሰው ስለሚመጡ፥ የወደፊት ተስፋ አላችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ወደ ፊት ተስፋ አለሽ” ይላል እግዚአብሔር። “ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለወደፊት ላለሽ ጊዜ ተስፋ አለሽ፥ ይላል ጌታ፥ ልጆችሽም ወደ ግዛታቸው ይመለሳሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለፍ​ጻ​ሜ​ሽም ተስፋ አለ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ልጆ​ች​ሽም ወደ ሀገ​ራ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቸው ይመለሳሉ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 31:17
19 Referencias Cruzadas  

ከዐሥሩ አንድ ክፍል ቢተርፍም እንኳ እርሱም እንደ ግራር ወይም እንደ ዋርካ እንደገና ይቃጠላል። ዛፉ ሲቈረጥ ጉቶው ይቀራል። ጉቶውም የተቀደሰ ዘር ነው።”


ስለዚህ፦ “ክብሬ ተለይቶኛል፤ ከእግዚአብሔር የምጠብቀውም ተስፋ ሁሉ ተቋርጦአል” አልኩ።


ሆኖም ይህን አንድ ነገር በማስብበት ጊዜ በተስፋ እሞላለሁ።


ሰው የእግዚአብሔርን አዳኝነት ጸጥ ብሎ መጠበቁ መልካም ነው።


እንደገና ተስፋ ሊኖር ስለሚችል ራሱን ዝቅ አድርጎ ያስገዛ።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕዝቤን ሁሉ ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል በአንድነት ሰብስቤ ወደገዛ ምድራቸው መልሼ የማመጣቸው መሆኔን ንገራቸው።


ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል።


ተማርከው ወደ ስደት እንዲሄዱ ያደረግኋቸው እኔ ብሆንም እንኳ አሁን ከእነርሱ አንድም ሰው ወደኋላ ሳይቀር ወደ ገዛ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጌአለሁ። ስለዚህ ሕዝቤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው መሆኔን ያውቃሉ።


የቀድሞውን የወይን ተክል እመልስላታለሁ፤ የመከራንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤ እዚያም ከግብጽ ስትወጣ በወጣትነትዋ ወራት በነበራት ሁኔታ በደስታ ትዘምራለች።


ከዚህ ጊዜ በኋላ እስራኤላውያን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርና ወደ ንጉሣቸው ወደ ዳዊት ይመለሳሉ፥ በኋለኛው ዘመን በፍርሃት ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፤ በረከቱንም ይቀበላሉ።


እናንተ የተስፋ ባለቤት የሆናችሁ ምርኮኞች ሆይ! እኔ ዛሬ ቀድሞ ከነበራችሁ በእጥፍ ስለምሰጣችሁ፥ ወደ አምባችሁ ተመለሱ።


እነዚያ ቀኖች ባያጥሩማ ኖሮ አንድም ሰው መዳን ባልቻለ ነበር፤ ነገር ግን ስለ ተመረጡት ሰዎች እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ።