ስለ ፈጸማችሁት ኃጢአት አንተን ራስህን፥ ልጆችህንና መኳንንትህን ሁሉ እቀጣለሁ። አንተም ሆንክ የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ሕዝብ የሰጠኋችሁን ማስጠንቀቂያ ከምንም አልቈጠራችሁትም፤ ከዚህም የተነሣ አስቀድሞ ላመጣው ያቀድኩትን መቅሠፍት ሁሉ በእናንተ ላይ አመጣባችኋለሁ።’ ”
ኤርምያስ 23:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢይ ወይም ካህን ወይም ከሕዝቡ አንዱ ‘የእግዚአብሔር ሸክም’ ብሎ ከተናገረ እርሱንም ቤተሰቡንም እቀጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢይ ወይም ካህን ወይም ማንኛውም ሰው፣ ‘የእግዚአብሔር ሸክም’ እያለ ቢናገር፣ ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢይና ካህን ሕዝቡም ‘የጌታ ሸክም’ ብሎ ቢናገር፥ ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ሸክም የሚለውን ነቢይንና ካህንን፥ ሕዝብንም ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ሸክም የሚለውን ነቢይንና ካህንን ሕዝቡንም ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ። |
ስለ ፈጸማችሁት ኃጢአት አንተን ራስህን፥ ልጆችህንና መኳንንትህን ሁሉ እቀጣለሁ። አንተም ሆንክ የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ሕዝብ የሰጠኋችሁን ማስጠንቀቂያ ከምንም አልቈጠራችሁትም፤ ከዚህም የተነሣ አስቀድሞ ላመጣው ያቀድኩትን መቅሠፍት ሁሉ በእናንተ ላይ አመጣባችኋለሁ።’ ”
የእናንተ ነቢያት ሐሰተኛና አታላይ ራእይ አይተውላችኋል፤ ሐሰተኛና አሳሳች ትንቢት ተናገሩ እንጂ፥ ዕድል ፈንታችሁን ለመለወጥ በደላችሁን አላጋለጡም።
ማንም ነቢይ ነኝ ብሎ ቢነሣ የወለዱት አባቱና እናቱ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ስለ ተናገርክ መሞት አለብህ ይሉታል፤ ትንቢትም ሲናገር ወላጆቹ ወግተው ይገድሉታል።