ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጒዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “እግዚአብሔር ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።
ኤርምያስ 20:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን! እናቴ እኔን የወለደችበትም ዕለት የተባረከ አይሁን! አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተወለድሁባት ዕለት የተረገመች ትሁን፤ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን አትባረክ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን! እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተወለድሁባት ቀን፥ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተረገመች ትሁን፤ የተባረከችም አትሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን፥ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን። |
ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጒዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “እግዚአብሔር ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምን ወለድሽኝ? ዕድል ፈንታዬ ከአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ጋር መከራከርና መነታረክ ሆኗል፤ እኔ ገንዘብ ለማንም አላበደርኩም ወይም ከማንም አልተበደርኩም፤ ሆኖም ሰው ሁሉ ይረግመኛል።