ኤርምያስ 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም እግዚአብሔር “ሌላስ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “በስተ ሰሜን በኩል አንድ ማሰሮ ሲፈላ አያለሁ፤ ወደዚህም ለመገልበጥ አዘንብሎአል” ስል መለስኩለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳግመኛም የእግዚአብሔር ቃል፣ “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም፣ “አንድ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደዚህ ያዘነበለ ነው” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለተኛም ጊዜ የጌታ ቃል “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም “የሚፈላ የሸክላ ድስት ከሰሜን ፊቱን አዘንብሎ አያለሁ” አልሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፥ “ምን ታያለህ?” እኔም፥ “የሚፈላ አፍላል አያለሁ፤ ፊቱም ወደ ሰሜን ወገን ነው” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል፦ ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም፦ የሚፈላ አፍላል አያለሁ፥ ፊቱም ከሰሜን ወገን ነው አልሁ። |
እግዚአብሔርም “ኤርምያስ ሆይ! ይህ የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም “እነሆ የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ ፍሬዎች እጅግ የተዋቡ ናቸው፤ መጥፎዎቹ ፍሬዎች ደግሞ ለምግብነት ደስ የማይሉና እጅግ የተበላሹ ናቸው” ስል መለስኩለት።
‘እንደገና መልሰን ቤቶችን የምንሠራበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፤ ከተማይቱ እንደ ሥጋ መቀቀያ ሰታቴ ስትሆን፥ እኛ ደግሞ በውስጥዋ እንደ ሥጋ ሆነናል’ ብለዋል።
“ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምላችሁ ይህ ነው፦ ‘በሰታቴው ውስጥ ያለው ሥጋ እናንተ የገደላችኋቸው ሰዎች ናቸው፤ ይህችም ከተማ ሰታቴዋ ነች፤ እናንተ ግን ከከተማይቱ ትወገዳላችሁ።
ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የምላቸውን ንገራቸው፤ እኔ የተናገርኩት ሁሉ ይፈጸማል፤ ከቶም አይዘገይም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።”
እግዚአብሔርም “ይህ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልኩት። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ እነርሱን ከመቅጣት አልመለስም።
“ይህ የምታየው ምንድን ነው?” ብሎም ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት፦ “ሰባት መብራቶች ያሉበት አንድ የወርቅ መቅረዝ አያለሁ፤ በአናቱም ላይ የዘይት ማሰሮ አለ፤ ሰባቱም መብራቶች የክር ማስተላለፊያ ቧንቧ አላቸው።