ያዕቆብ 4:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ፤ ሰውን የሚያማ ወይም በሰው ላይ የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል፤ በሕግ ላይ ብትፈርድ ደግሞ ፈራጅ መሆንህ ነው እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ እርስ በርሳችሁ አትወነጃጀሉ፤ ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙም ላይ የሚፈርድ በሕግ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል። በሕግ ላይ ብትፈርድ ፈራጅ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትወነጃጀሉ፤ ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙም ላይ የሚፈርድ በሕግ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል። በሕግ ላይ ብትፈርድ ፈራጅ እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። |
“በማንም ላይ አትፍረዱ፤ በእናንተም ላይ አይፈረድባችሁም፤ ሌሎችን አትንቀፉ፤ እናንተም አትነቀፉም፤ ይቅር በሉ፤ እናንተም ይቅርታ ታገኛላችሁ፤
በሌላው ሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ለራስህ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ሰው ላይ ስትፈርድ በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ አንተ በሰው ላይ እየፈረድክ፥ ያ የፈረድክበት ሰው የሚያደርገውን ታደርጋለህ።
እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ራሱ ኃጢአት ነውን? አይደለም! ነገር ግን ኃጢአት ምን መሆኑን እንዳውቅ ያደረገኝ ሕግ ነው። ሕግ “አትመኝ” ባይል ኖሮ ምኞት ምን መሆኑን ባላወቅሁም ነበር።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
እኔ ወደዚያ በምመጣበት ጊዜ ምናልባት ልትሆኑ እንደምፈልገው ሳትሆኑ፥ እኔም እናንተ እንደምትፈልጉት ሳልሆን እንገናኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ፤ እንዲሁም በእናንተ ዘንድ ጥል፥ ቅናት፥ ቊጣ፥ ራስ ወዳድነት፥ የሰው ስም ማጥፋት፥ ሐሜት፥ ትዕቢትና ሁከት ይኖሩ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ።
እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በጠባያቸው የተከበሩ እንዲሆኑ እንጂ ሐሜተኞችና፥ የመጠጥ ሱሰኞች እንዳይሆኑና መልካሙን ትምህርት እንዲያስተምሩ ምከራቸው።
ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ መርምሮ በእርሱ የሚጸና፥ እርሱንም ሰምቶ መርሳት ሳይሆን፥ በሥራ ላይ የሚያውለው ሰው በሥራው የተባረከ ይሆናል።
ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ጌታ እስኪመጣ ድረስ በትዕግሥት ጠብቁ፤ ገበሬ መሬቱ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን ዝናብ እስከሚያገኝ እየታገሠ ክቡር ዋጋ ያለውን የመሬቱን ፍሬ ይጠባበቃል።