ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።
ኢሳይያስ 66:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ይላል፦ “የመውለጃዋ ጊዜ እንዲደርስ ያደረግኋትን ሴት ልጅዋን እንዳትወልድ አደርጋለሁን? እንድትፀንስ ያደረግኋትን ሴት ማሕፀኗን እዘጋለሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊወለድ የተቃረበውን፣ እንዳይወለድ አደርጋለሁን?” ይላል እግዚአብሔር። “በሚገላገሉበት ጊዜስ፣ ማሕፀን እዘጋለሁን?” ይላል አምላክሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ወደ መውለድ የማደርስ እኔ እንዳይወለድ አደርጋለሁን? ይላል ጌታ፤ ሊወልድ የተቃረበውን ማኅፀንን እኔ እዘጋለሁን? ይላል አምላክሽ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ተስፋን ሰጠሁሽ፤ አንቺ ግን አላሰብሽኝም ይላል እግዚአብሔር። ሴት እንድትወልድ፥ መካንም እንዳትሆን የማደርግ እኔ አይደለሁምን?” ይላል አምላክሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ወደ መውለድ የማደርስ እኔ አላስወልድምን? ይላል እግዚአብሔር፥ የማስወልድስ ማኅፀንን እኔ እዘጋለሁን? ይላል አምላክሽ። |
ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።
እነርሱም ከሕዝቅያስ ተቀብለው ለኢሳይያስ የነገሩት መልእክት ይህ ነበር፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤