እናውቀው ዘንድና ትክክል ነው እንል ዘንድ ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህን የተናገረ ማነው? ስለዚህ ጉዳይ መግለጫ የሰጠ፥ ወይም ያወጀ፥ ከእናንተም አንድ ቃል የተናገረ የለም።
ኢሳይያስ 41:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጣዖቶቻችሁንም አምጡና በሚፈጸምበት ጊዜ እንድናውቀው ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ይንገሩን፤ ወደፊት ውጤታቸው ምን እንደሚሆን አስተውለን እንረዳ ዘንድ የቀድሞዎቹ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ይንገሩን፤ ወይም ወደፊት ምን እንደሚከሠት ያስረዱን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሚሆነውን እንዲነግሩን፣ ጣዖቶቻችሁን አምጡ፤ እንድንገነዘብ፣ ፍጻሜአቸውን እንድናውቅ፣ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ነበሩ ንገሩን፤ ስለሚመጡትም ነገሮች ግለጹልን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፤ ልብም እድናደርግ፥ ፍጻሜአቸውንም እድናውቅ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ተናገሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይምጡ፤ የሚደርስባችሁንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ፤ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ንገሩን፤ የሚመጡትንም አሳዩን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፥ ልብም እናደርግ ዘንድ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደሆኑ ተናጋሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን። |
እናውቀው ዘንድና ትክክል ነው እንል ዘንድ ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህን የተናገረ ማነው? ስለዚህ ጉዳይ መግለጫ የሰጠ፥ ወይም ያወጀ፥ ከእናንተም አንድ ቃል የተናገረ የለም።
እነሆ፥ እኔ አስቀድሜ የተናገርኳቸው ነገሮች ሁሉ ተፈጽመዋል፤ አሁን ደግሞ ወደ ፊት ስለሚሆኑት አዳዲስ ነገሮች፥ ከመፈጸማቸው በፊት እናገራለሁ።”
እንደ እኔ ያለ ማነው? እስቲ ካለ ይናገር፤ እስቲ ማስረጃውን በፊቴ ያቅርብ፤ ወደፊት የሚሆነውን አስቀድሞ የተናገረ ማነው? እስቲ ወደፊት የሚሆነውን ይናገር።
ጉዳይህን አቅርበህ ገለጻ አድርግ፤ ከብዙ ጊዜ በፊት ይህን የተናገሩ ተሰብስበው ይመካከሩ፤ በጥንት ጊዜ የተናገረው ማነው? እኔ እግዚአብሔር አልነበርኩምን? ከእኔ በቀር ጻድቅና አዳኝ አምላክ የለም።
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።
“ሁላችሁም ተሰብስባችሁ ኑና አድምጡ! ስለ እነዚህ ነገሮች አስቀድሞ የተናገረ ከጣዖቶች መካከል የትኛው ነው? የእግዚአብሔር ተመራጭ በባቢሎን ላይ ዓላማውን ይፈጽማል። ኀይሉም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።
እግዚአብሔር ለእስራኤል እንዲህ ይላል፦ “ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር ከብዙ ጊዜ በፊት ተናገርኩ፤ እርሱንም በፍጥነት እንዲከናወን አደረግሁ።