ኢሳይያስ 40:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ ዘር የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! “አካሄዴ ከእግዚአብሔር የተሰወረ ነው፤ መብቴም በእርሱ ዘንድ ችላ ተብሎብኛል፤” ብለህ ለምን ታማርራለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትላለህ? እስራኤል ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትናገራለህ? “መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፤ ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤል ሆይ፦ “መንገዴ ከጌታ ተሰውራለች፥ ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፥ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፤ አምላኬም ከእኔ ርቋል፤ ፍርዴንም ትትዋል፤ ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤል ሆይ፦ መንገድህ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? |
አምላክ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ አንተ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን አድርገሃል፤ ከጥንት ጀምሮ ያቀድከውን ሁሉ፥ ፍጹምነት ባለው አስተማማኝ ሁኔታ አከናውነሃል።
እኔ ግን “በከንቱ ለፋሁ፤ ያለ ጥቅም በከንቱ ጒልበቴን አባከንሁ፤ ሆኖም ጉዳዬ በእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ የድካሜም ዋጋ ከአምላኬ ጋር ነው” አልኩ።
ዳዊት በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፤ “አንድ ቀን ሳኦል እኔን ይገድለኛል፤ እንግዲህ ለእኔ የሚበጀኝ ነገር አምልጬ ወደ ፍልስጥኤም መሄድ ነው፤ ከዚያም በኋላ ሳኦል በእስራኤል ምድር እኔን መፈለጉን ስለሚተው ከእጁ አመልጣለሁ።”