ሮብዓም እነዚህን ከተሞች አጠንክሮ መሸገ፤ ለእያንዳንዳቸውም አንዳንድ የከተማ ኀላፊ ሾመ፤ በእያንዳንዳቸውም ውስጥ እህል፥ የወይራ ዘይትና የወይን ጠጅ፥
ኢሳይያስ 22:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ሁሉ እየተዘዋወራችሁ ቈጠራችሁ፤ ቅጥሩን ለማደስ አንዳንዶቹን ቤቶች አፈረሳችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢየሩሳሌምን ቤቶች ቈጠራችሁ፥ ቅጥሩንም ለመጠገን ቤቶችን አፈረሳችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ቈጠራችሁ፤ ቅጥሩንም ለማጽናት ቤቶችን አፈረሳችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢየሩሳሌምን ቤቶች ቈጠራችሁ፥ ቅጥሩንም ለማጥናት ቤቶችን አፈረሳችሁ። |
ሮብዓም እነዚህን ከተሞች አጠንክሮ መሸገ፤ ለእያንዳንዳቸውም አንዳንድ የከተማ ኀላፊ ሾመ፤ በእያንዳንዳቸውም ውስጥ እህል፥ የወይራ ዘይትና የወይን ጠጅ፥
ከጥንቱ ኲሬ የሚወርደውን ውሃ ለመመለስ በከተማይቱ ውስጥ ግድብ ሠራችሁ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በመጀመሪያ ዐቅዶ ያደረገው እግዚአብሔር መሆኑ ትዝ አላላችሁም።
እግዚአብሔርም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፦ “አንተና ልጅህ ሼርያሹብ ንጉሥ አካዝን ለመገናኘት ውጡ፤ እርሱንም ከላይኛው ኩሬ ውሃ በሚመጣበት በልብስ አጣቢዎች ቦታ ታገኙታላችሁ።
ለጦሩ ወደ አሞናውያን ከተማ ራባ በሚወስደው መንገድ ላይና እንዲሁም ወደ ተመሸገችው የይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ላይ የአቅጣጫ ምልክት አድርግ።