ዘበኛውም ድምፁንም በማሰማት ያየውን ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ፤ ያም ሯጭ ሰው እየቀረበ መጣ።
ኢሳይያስ 21:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ሂድ ሁኔታውን ሁሉ እያጠና የሚገልጥልህ ተመልካች መድብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እንዲህ አለኝ፤ “ሂድ፤ ጠባቂ አቁም፤ ያየውንም ይናገር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ ሂድ ጉበኛም አቁም፥ የሚያየውንም ይናገር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛልና፥ “ፈጥነህ ሂድ፤ ጕበኛንም አቁም፤ የሚያየውንም ይናገር፤ የሚሰማውንም ያውራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ ሂድ ጕበኛም አቁም፥ የሚያየውንም ይናገር። |
ዘበኛውም ድምፁንም በማሰማት ያየውን ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ፤ ያም ሯጭ ሰው እየቀረበ መጣ።
“የሰው ልጅ ሆይ! እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ጠባቂ አድርጌሃለሁ፤ ስለዚህ እኔ የምናገረውን ቃል ስማ፤ የምሰጥህንም የማስጠንቀቂያ ቃል ንገራቸው።