ረጃጅም የከተማ መጠበቂያ ግንቦችንና የጦር ምሽጎችን ሁሉ ዝቅ ያደርጋል፤
ረዣዥሙን ግንብ ሁሉ፣ የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፣
ረጃጅሙን ግንብ ሁሉ፤ የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፤
በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፥ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፥
በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፥ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፥
እንደ ዋነተኛ እጆቻቸውን ይዘረጋሉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በትዕቢታቸው ስለሚያዋርዳቸው እጆቻቸው ይዝለፈለፋሉ።
የሞአብን ምሽጎች ከታላላቅ ግንቦቻቸው ጋር ያፈራርሳል፤ ተሰባብረውም ከትቢያ ጋር ይቀላቀላሉ።
በሕዝቡ ላይ እልቂት በሚደርስበት ጊዜ ከታላላቅ ተራራዎችና ከከፍተኛ ኰረብቶች የምንጭ ውሃ ይፈስሳል።
በዚያን ቀን በተመሸጉት ከተሞችና በረጃጅም ግንቦች ላይ የጦርነት መለከትና የማስጠንቀቂያ ድምፅ ይሰማል።