ዕብራውያን 5:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም እግዚአብሔር በመልከ ጼዴቅ የክህነት ሹመት ዐይነት የካህናት አለቃ አድርጎ ሾመው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመትም ሊቀ ካህናት ተብሎ በእግዚአብሔር ተሾመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔርም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ተጠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘለዓለም ሊቀ ካህናት አለው። |
ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ።