ዘፍጥረት 8:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባት ቀን ከቈየም በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ኖኅ ርግቧን እንደ ገና ላካት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀን ከቈየም በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግብን እንደገና ከመርከብ ላካት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ ደግሞ እስከ ስባት ቀን ቆየ ርግንም እንደ ገና ከመርከብ ሰደደ። |
እርስዋም ወደ ማታ ጊዜ የለመለመ የወይራ ዘይት ዛፍ ቅጠል በአፍዋ ይዛ ወደ ኖኅ ተመለሰች፤ በዚህ ሁኔታ ኖኅ ውሃው ከምድር መጒደሉን ዐወቀ።
ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለ ነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ ውስጥ አስገባት።