ዘፍጥረት 6:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርዝመቱን 133 ሜትር፥ የጐኑን ስፋት 22 ሜትር፥ የከፍታውን ቁመት 13 ሜትር አድርግ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ መቶ አርባ ሜትር፣ ወርዷ ሃያ ሦስት ሜትር፣ ከፍታዋ ዐሥራ ሦስት ነጥብ ዐምስት ሜትር ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወርድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ አድርግ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መርከብዋንም እንዲህ ታደርጋታለህ፤ የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወርድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋንም እንዲህ ታደርጋታለህ የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፤ ወርድዋ አምሳ ክንድ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን። |
ለመርከቡ ጣራ አብጅለት፤ ጣራውና ግድግዳው በሚጋጠሙበት ቦታ ላይ 44 ሳንቲ ሜትር ባዶ ቦታ ተውለት፤ መርከቡ ባለሦስት ፎቅ እንዲሆን አድርግ፤ በጐኑም በኩል በር አድርግለት፤
ከረፋያውያን ወገን ንጉሥ ዖግ የመጨረሻው ነበር፤ አልጋው ከብረት የተሠራ ሆኖ በይፋ በታወቀው መለኪያ ቁመቱ አራት ሜትር፥ የጐኑም ስፋት ሁለት ሜትር ያኽል ነበር። እርሱም ራባ ተብላ በምትጠራው በዐሞናውያን ከተማ እስከ አሁን ይታያል።