አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሒታዊው ከዔፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።
ዘፍጥረት 50:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለቀብር አጅበውት ከሄዱት ሰዎች ሁሉ ጋር ሆኖ ወደ ግብጽ ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ፣ ከወንድሞቹና ለአባቱ ቀብር ዐብረውት ሄደው ከነበሩት ሁሉ ጋራ ወደ ግብጽ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍና ወንድሞቹ አባቱንም ሊቀብሩ ከእርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ሁሉ አባቱን ከቀበረ በኋላ ወደ ግብጽ ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍና ወንድሞቹ፥ አባቱንም ሊቀብሩ ከእርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ሁሉ አባቱን ከቀበረ በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍና ወንድሞቹ አባቱንም ሊቀብሩ ከእርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ሁሉ አባቱን ከቀበር በኍላ ወደ ግብፅ ተመለሱ። |
አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሒታዊው ከዔፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።
የዮሴፍ ወንድሞች አባታቸው ከሞተ በኋላ “ዮሴፍ ባደረስንበት በደል ሁሉ እስከ አሁንም ቂም ይዞ ሊበቀለን ቢፈልግ ምን እናደርጋለን?” ተባባሉ።