ቀጥሎም አጥንቶቻቸው እስከሚታይ ድረስ የከሱ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ እንደ እነርሱ የሚያስከፉ ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም።
ዘፍጥረት 41:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም አጥንታቸው እስከሚታይ የከሱ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወንዙ ዳር ከነበሩት ላሞች አጠገብ ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም መልካቸው የከፋ ዐጥንታቸው የወጣ፣ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጥሎም መልካቸው የከፋ ዐጥንታቸው የወጣ፥ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በኋላ እነሆ፥ መልካቸው የከፋ፥ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ተሰማርተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም በኍላ እነሆ መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዝ ወጡ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ይቆሙ ነበር። |
ቀጥሎም አጥንቶቻቸው እስከሚታይ ድረስ የከሱ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ እንደ እነርሱ የሚያስከፉ ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም።