24 ጒልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።
24 ከጾም የተነሣ ጕልበቴ ዛለ፤ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ።
24 ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ፥ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።
ስለዚህ የዛሉትን እጆቻችሁንና የደከሙትን ጒልበቶቻችሁን አበርቱ።
እዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ።
ጒልበቴ ደክሞ እንደ ውሃ ፈሰሰ፤ አጥንቶቼ ሁሉ ከመገጣጠሚያቸው ተለያዩ፤ ልቤም እንደ ሰም በውስጤ ቀለጠ።
ብዙ ሥራና ድካም ነበረብኝ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ በራብና በውሃ ጥም ተጨንቄአለሁ፤ ብዙ ጊዜም የምግብ እጦት ደርሶብኛል፤ ብርድና መራቆትም ደርሶብኛል።
በምጾምበት ጊዜ በጣም አለቀስኩ፤ በዚህም ተሰደብኩ።
ሥጋዬ አልቆ ቆዳዬ በአጥንቴ ላይ ተጣበቀ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ ተረፍኩ።
የሐዘን ልብስ ስለብስ እየተዘባበቱ ይስቁብኛል።