ዘፍጥረት 4:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጺላም “ቱባልቃይን” የተባለ ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሱ ከነሐስና ከብረት ልዩ ልዩ ዐይነት ዕቃዎችን ይሠራ ነበር። ቱባልቃይንም ናዕማ የተባለች እኅት ነበረችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጺላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም እኅት ናዕማ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴላም ደግሞ ቶቤልን ወለደች። እርሱም ናስና ብረትን የሚሠራ ሆነ። የእኅቱም ስም ኖሄም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች፤ የቱባልቃይንም እኅት ናዕማ ነበረች። |
ላሜክ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤ እናንተ “ዓዳ እና ጺላ የላሜክ ሚስቶች ሆይ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ የምለውን ስሙ፤ አንድ ወጣት መትቶ ስላቈሰለኝ ገደልኩት፤
እንግዲህ ቅርጽን የማውጣት፥ ወርቅን፥ ብርን፥ ነሐስንና ብረትን የማቅለጥ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ልብስ የመሥራት ችሎታ ያለውን ብልኀተኛ ሰው ላክልኝ፤ እርሱም አባቴ ዳዊት ከመረጣቸው በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልኀተኞች ሰዎች ጋር ይሠራል።
እንደ ወርቅ፥ ብር፥ ነሐስ፥ ብረት፥ ቆርቆሮ ወይም እርሳስ የመሳሰሉ እሳት የማይጐዳቸው ነገሮች በእሳት ውስጥ አልፈው መጥራት ይኖርባቸዋል፤ እሳት መቋቋም የማይችለውን ነገር ሁሉ ለመንጻት ሥርዓት በተመደበው ውሃ ታጠሩታላችሁ።