ሰውየውም እዚያ የሚኖሩትን ሰዎች “በዔናይም ደጅ በመንገድ ዳር የነበረችው አመንዝራ ሴት ወዴት ሄደች?” ብሎ ጠየቀ። ሰዎቹም “በዚህ አካባቢ እንደዚህ ያለች አመንዝራ ሴት የለችም” አሉት።
ዘፍጥረት 38:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰውየው ወደ ይሁዳ ተመልሶ ሄደና “ላገኛት አልቻልኩም፤ በዚያ የሚኖሩትም ሰዎች ‘እንደዚህ ያለች አመንዝራ ሴት እዚህ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልእክተኛውም ወደ ይሁዳ ተመልሶ፣ “ሴቲቱን ላገኛት አልቻልሁም፤ ነዋሪዎቹም ‘በዚህ አካባቢ እንደዚህች ያለች ዝሙት ዐዳሪ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልእክተኛውም ወደ ይሁዳ ተመልሶ፥ “ሴቲቱን ላገኛት አልቻልኩም፤ ነዋሪዎቹም ‘በዚህ አካባቢ እንደዚህች ያለች ዝሙት ዐዳሪ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ይሁዳም ተመልሶ እንዲህ አለው፥ “አላገኘኋትም፤ የሀገሩ ሰዎች ደግሞ፦ ከዚህ ዘማ የለችም” አሉኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ በዚህ ጋለሞታ አልነበረችም አሉት። ወደ ይሁዳም ተመልሶ እንዲህ አለው፦ አላገኘኍትም የአገሩም ሰዎች ደግሞ፦ ከዚህ ጋለሞታ አልነበረችም አሉኝ። |
ሰውየውም እዚያ የሚኖሩትን ሰዎች “በዔናይም ደጅ በመንገድ ዳር የነበረችው አመንዝራ ሴት ወዴት ሄደች?” ብሎ ጠየቀ። ሰዎቹም “በዚህ አካባቢ እንደዚህ ያለች አመንዝራ ሴት የለችም” አሉት።
ይሁዳም “እንግዲህ ጠቦቱን ልኬላት ነበር፤ ነገር ግን ልታገኛት አልቻልክም፤ ስለዚህ ሰዎች መሳቂያ እንዳያደርጉን የወሰደችውን መያዣ እዚያው ታስቀረው” አለ።