ስለዚህ ትዕማር የመበለትነት ልብሷን ለውጣ ፊቷን በሻሽ ሸፈነች፤ ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ዳር በዔናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ይህንንም ያደረገችው ሴላ አድጎ ሳለ ለእርሱ በሚስትነት እንድትሰጥ አለመፈቀዱን ስለ ተረዳች ነው።
ዘፍጥረት 38:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ሻሽዋን ከፊቷ ላይ አንሥታ የመበለትነት ልብሷን እንደገና ለበሰች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሿን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፥ ሻሽዋን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ተነሥታ ሄደች፤ መጐናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነቷን ልብስ ለበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤስውም ተነሥታ ሄደች መጎናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነትዋን ልብስ ለበስች። |
ስለዚህ ትዕማር የመበለትነት ልብሷን ለውጣ ፊቷን በሻሽ ሸፈነች፤ ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ዳር በዔናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ይህንንም ያደረገችው ሴላ አድጎ ሳለ ለእርሱ በሚስትነት እንድትሰጥ አለመፈቀዱን ስለ ተረዳች ነው።
እርሱም “ታዲያ፥ መያዣ የሚሆን ነገር ምን ልስጥሽ?” አላት። እርስዋም “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያውና ይህን የያዝከውን በትር ስጠኝ” አለችው። ስለዚህ የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና ወደ እርስዋ ገባ፤ እርስዋም ፀነሰችለት
ይሁዳ በመያዥያ መልክ የሰጣትን ነገሮች ለማስመለስ የፍየል ጠቦት በዐዱላማዊው ሰው እጅ ወደ ሴትዮዋ ላከ፤ ሰውየው ግን ሊያገኛት አልቻለም።
ስለዚህም በተቆዓ የምትኖረውን አንዲት ብልኅ ሴት አስጠራ፤ እርስዋም በደረሰች ጊዜ “ሐዘንተኛ ለመምሰል ሞክሪ፤ የሐዘን ልብስሽን ልበሺ፤ ቅቤም አትቀቢ፤ ለብዙ ጊዜ በሐዘን ላይ የቈየሽ ሴት ለመምሰል ተዘጋጂ፤