ዘፍጥረት 37:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን መንጋዎች ይዘው ወደ ሴኬም ተሰማሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በኋላ የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማሰማራት ወደ ሴኬም አካባቢ ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቹ በሴኬም የአባታቸውን በጎች ይጠብቁ ዘንድ ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቹም በሴኬም የአባታቸውን በጎች ይጠብቁ ዘንድ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቹ በሴኬም የአባታቸውን በጎች ይጠብቁ ዘንድ ሄዱ። |
እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ።
‘እኛ ልክ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የምንተዳደረው በግ በማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። በግ አርቢዎች በግብጻውያን ዘንድ የተናቁ ስለ ሆኑ ይህን በመናገር በጌሴም ምድር ለመኖር ፈቃድ ታገኛላችሁ።”
ከሴኬም፥ ከሴሎና ከሰማርያ ሰማኒያ ሰዎች በድንገት መጡ፤ እነርሱም በሐዘን ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውን ቀደው፥ ፊታቸውን ነጭተው ነበር፤ ለቤተ መቅደስም መባ የሚያቀርቡትን እህልና ዕጣን ይዘው ነበር፤