አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”
ዘፍጥረት 37:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ተቀማጭነቱን አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም አባቱ በስደት በኖረበት አገር በከነዓን ምድር ተቀመጠ።። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም አባቱ በስደት በኖረበት ሀገር በከነዓን ምድር ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም አባቱ በስደት በኖረበት አገር በከነዓን ምድር ተቀመጠ። |
አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን ይህችን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ መላውን የከነዓን ምድር ለዘለዓለም እንዲወርሱት ለዘርህ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”
አብርሃምን እንደ ባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ! ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ስደተኛ ሆነህ የኖርክበትን ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ!”
ይህንንም ያደረገበት ምክንያት እርሱና ያዕቆብ ብዙ ንብረት ስለ ነበራቸው፥ የሚሰፍሩበት ምድር ለሁለት ስላልበቃ ነው፤ ሁለቱም ብዙ እንስሶች ስለ ነበሩአቸው አብረው ለመኖር አልቻሉም።