እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ እኔ በደረስኩበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር በረከትን ሰጥቶሃል፤ የምሠራውስ መቼ ለቤተሰቤ የሚጠቅም ነገር ነው?” አለው።
ዘፍጥረት 30:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም “ታዲያ ምን ያኽል ልክፈልህ?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ የምልህን አንድ ነገር ብቻ ብታደርግልኝ መንጋህን ማሰማራቴንና መጠበቄን እቀጥላለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም፣ “ታዲያ ምን ልስጥህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ምንም አትስጠኝ፤ ነገር ግን የምጠይቅህን አንዲት ነገር ብቻ ብታደርግልኝ ከብቶችህን ማገዴን እቀጥላለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “የምሰጥህ ምንድነው?” አለ። ያዕቆብም አለው፦ “ምንም አትስጠኝ፥ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደገና በጎችህን አበላለሁ እጠብቃለሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም፥ “የምሰጥህ ምንድን ነው?” አለው። ያዕቆብም አለው፥ “ምንም አትስጠኝ፤ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደገና በጎችህን አሰማራለሁ፤ እጠብቃለሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ የምሰጥህ ምንድር ነው? አለ። ያዕቆብም አለው፦ ምንም አትስጠኝ፤ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደ ገና በጎችህን አበላለሁ እጠብቃለሁም። |
እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ እኔ በደረስኩበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር በረከትን ሰጥቶሃል፤ የምሠራውስ መቼ ለቤተሰቤ የሚጠቅም ነገር ነው?” አለው።
ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጒርጒርና ነቊጣ፥ ጥቊርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቊጣና ዝንጒርጒር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤