እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው።
ዘፍጥረት 30:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና ብላ ጠራቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ሴት ልጅን ወለደች፥ ስምዋንም ዲና አለቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ሴት ልጅን ወለደች፤ ስምዋንም ዲና አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ ሴት ልጅን ወለደች፤ ስምዋንም ዲና አለቻት። |
እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው።
እነዚህ ወንዶች ልጆችና ሴቷም ልጅ ዲና በመስጴጦምያ ሳሉ ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ናቸው። ያዕቆብ ከልያ ያፈራቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ሠላሳ ሦስት ናቸው።