ዘፍጥረት 3:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከርሷም ጋራ ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ጥበብ ለማግኘትም የሚመኙት እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም በላ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዐይንም ለማየት እንደሚያስጐመጅ፥ መልካምንም እንደሚያሳውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍሬው ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፤ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፤ ለጥበብም መልካም እንድ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስው ጋር በላ። |
አዳምንም እንዲህ አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘አትብላ’ ያልኩህን ፍሬ ከዛፉ ወስደህ ስለ በላህ፥ አንተ በፈጸምከው ክፉ ሥራ ምክንያት ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ምግብህን ከእርስዋ የምትበላው በብርቱ ድካም ነው።
አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤
“የሰው ልጅ ሆይ! የምትወዳትና የዐይንህ መደሰቻ የሆነችው ሚስትህ ተቀሥፋ በድንገት ትሞትብሃለች፤ በዚህም አትዘን፤ እንባህንም በማፍሰስ አታልቅስ፤
‘ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው አለኝ፤ የክብራችሁ ትምክሕት፥ የዐይናችሁ ተስፋና የልባችሁ ደስታ የሆነውን ቤተ መቅደሴን እንዲያረክሱ እተዋቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌም የቀሩት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በጦርነት ይገደላሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! ዘወትር ሊያዩትና ሊጐበኙት የሚወዱትን፥ የሚመኩበትንና የሚደሰቱበትን እጅግ ጽኑ የሆነውን ቤተ መቅደስ ከእነርሱ እወስድባቸዋለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም እወስዳለሁ።
ካገኘነው ዕቃ መካከል ውብ የሆነ የባቢሎናውያን ካባ፥ ሁለት ኪሎ ያኽል የሚመዝን ብርና ግማሽ ኪሎ ያህል የሚመዝን ምዝምዝ ወርቅ አየሁ፤ እነርሱንም ለማግኘት ብርቱ ፍላጎት ስላደረብኝ ወስጃቸዋለሁ፤ እነርሱንም ብሩ ከታች ሆኖ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተቀብረዋል።”
ከዚህም የተነሣ እርስዋ በሠርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ አለቀሰች፤ አጥብቃም ስለ ነዘነዘችው የእንቆቅልሹን ፍች በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርስዋም ሄዳ ለፍልስጥኤማውያኑ ነገረቻቸው።